መለስ፣ የብሄረሰብ እኩልነት ጥያቄና ግንቦት 20
(በብርሃኑ አባዲ) [From Aiga forum]
የታላቁ መሪ የመለስ ዜናዊ ሕዝባዊ ትግል “ሀ” ብሎ የሚጀምረው ከተማሪዎች ንቅናቄ የትግል
ታሪክ ነው፡፡ እርግጥ ነው የመለስ ሁሉንም ዓይነት ጭቆናዎች የመቃወም ዝንባሌ ገና ከልጅነቱ
እንደሚጀምር የታሪክ ማህደሩ ያስረዳል፡፡ ሆኖም ግን በተደራጀ እና የበለጠ ብስለት ባለው ሁኔታ
የንቅናቄው ተዋናይ መሆን የቻለው ከቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትግል ጋር በተያያዘ
መሆኑ ሊጤን ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ከተቀሰቀሰ ከ1951 ዓ.ም.በኋላ ወደ ላቀ ደረጃ የተሸጋገረው ከአሥር
ዓመት በኋላ በ1961 ዓ.ም. እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ይህ ወቅት ለዘብተኞቹ የንቅናቄው
አባሎች በሥር ነቀል ለውጥ አራማጆች ተፅዕኖ ሥር የወደቁበትና መሠረታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች
ጎልተው የወጡበት ነው፡፡
ቀደም ባሉት ጊዜያት በጥቅሉ ይቀነቀን የነበረው የፖለቲካ ጥያቄ የዘውዳዊው ሥርዓት መገርሰስና
በምትኩም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሰረት የሚያመላክት ነበር፡፡ በወቅቱ እጅግ ትኩረት
ካገኙት መፈክሮች የአብዛኛውን ድጋፍ ያገኘናተደጋግሞ የተስተጋባውመፈክር “የመሬት ላራሹ”
ጥያቄ እንደነበር በግልፅ ይታወቃል፡፡ አብዛኛውን የአገሪቱን ሕዝብ የሚሸፍነውን እና እጅግ
አንገብጋቢ የሆነውን የመሬት ጥያቄ ማንሳት ተገቢነት እንደነበረውም ለአብዛኛው ያስማማል፡፡
ሆኖም ከመሬት ጥያቄ በትይዩ ሁሉንም የአገሪቱን ሕዝቦች የሚነካውና የሥርዓቱን ኢ-ፍትሃዊነት
በእጅጉ የሚያጋልጠውን የብሄሮች እኩልነት ጥያቄ ደፍሮ ማንሳት ያልተቻለበት ሁኔታ ነበር፡፡
ከ1961 ዓ.ም. በኋላ ግን የቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ንቅናቄ በሥር ነቀል ተራማጅ
ተማሪዎች ተፅዕኖ ሥር መውደቅ በመጀመሩ የብሄረሰብ እኩልነት ጥያቄ በድፍረት ይቀነቀን
ጀመር፡፡
Here is the full Pdf

No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.